የሀዘን መግለጫ

የማህፀንና ፅንስ ሀኪም የነበሩት ዶ/ር ዮናስ ጌታቸው ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ማክሰኞ ጥቅምት 17፣ 2013 ዓ.ም ምሽት ሕይወታቸው አልፏል።ትላንት ከ8 ሰአት ጀምሮ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአስክሬን ሽኝት ፕሮግራም የተደረገላቸው ሲሆን የቀብር ስነ ስርአቱ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ዶ/ር ዮናስ ጌታቸው

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር በዶ/ር ዮናሰ ጌታቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰባቸውና ለወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናትን ይመኛል፡፡