የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በሀገራችን ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኝ መልክ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ቫይረስን ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር በጤና ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች ድጋፍ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ማህበር ፣ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና መኮንኖች ማህበር ፣ የኢትጵያ ነርሶች ማህበርና ከኢትዮጵያ የአካባቢ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁንም በአዲስ አበባ ፣ በጎንደር ፣ በአርባምንጭ ፣ በሀሮማያና በደሴ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ለተወጣጡ 300 የጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በተያያዘም ከ20 የግል ጤና ተቋማት የተወጣጡና ከጡረታ ተመላሽ ለሆኑ 60 የጤና ባሙያዎች በኮቪድ-19 መከላከል ፣ መቆጣጠርና ህክምና ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
Ethiopian Medical Association is conducting “COVID-19 TOT” Program/Training in collaboration with the Ministry of Health (MoH) and other health professional associations in different regions of Ethiopia for quite a few Health professionals/workers who will be working in front lines in combating COVID-19. To date, the training has been provided to 300 health professionals from different parts of our country, in Addis Ababa, Gondar, Arbamich, Haromaya and Dessie. In addition, the associations are providing training on COVID-19 prevention, control and treatment for 60 health professionals from 20 private health organizations who have been retired and now returning back to work.