በቆዳና አባለዘር ህክምና ሰብ ስፔሻሊቲ ትምህርት ይጀመራል፡፡

ዶ/ር ዳኛቸው ሺበሺ

በጥቁር አንበሳ የጤና ሳይንስ ትምህርት ቤት የቆዳ እና አባለዘር ትምህርት ክፍል ሃላፊ

ሲጀመር…

የቆዳና አባለዘር ህክምና ትምህርትም ሆነ ህክምናው በአግባቡ በአገራችን በማይሰጥበት ዘመን ፖላንድ ነው የህክምና ዘርፉን ያጠኑት… “ለትምህር ከወጣሁ አይቀር” ብለውም ሰብ ስፔሻሊቲቸውን እና ፒ ኤች ዲ ያቸውን ሰርተው 1984 አካባቢ ነው የተመለሱት፡፡ 

ዶ/ር ዳኛቸው ወደ ህክምናው ዓለም ከመግባታቸው በፊት በ1950ዎቹ መጨረሻ አካባቢ መኮንንነት ኮርስ ወስደዋል ከዚያም ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል በመድፈኝነት አግለግለዋል፡፡ ይህን እየነገሩኝ ሳለ ታዲያ መቼ ነው ህክምናን ያጠኑት አልኳቸው… “አየሽ በሰራዊቱ ውስጥ እያለሁ ህክምናን የማጥናት ፍላጎት ነበረኝ የትምህርት ውጤቴም በጣም ጥሩ ነበር …ህክምናን ማጥናት እፈልጋለሁ አስተምሩኝ አልከኳቸው እነሱም ፈቀዱልኝ… አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገባሁ” አሉኝ፡፡

የቀይ ኮከብ ዘመቻ በሚባልበት ዘመን 1974 በአፋበትና በአቆርዳት በነበረው ጦርነት ዘምተዋል እንደ ወታደር ሳይሆን እንደ ሃኪም በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን በጠቅላላ ሃኪምነት አገልግለዋል ፡፡ “ከሁለቱም ወገን የምናገኘውን ቁስለኛ እናክማለን… ይሄ የኛ ያ የነሱ ነው አንልም” አሉኝ፡፡

በእርግጥ ህክምና ወገንተኛ አይደለም  ሰብዓዊነት እንጂ…

ደርማቶሎጂን ለምን መረጡት?

ብዙ ማውራት አይሆንላቸውም መሰል አጠር አጠር  አድረገው ነው የሚያጫውቱኝ….ያኔ ውጪ ስትሄጂ የነበረው ስፔሻሊቲ ሳይኪያትሪ ነበር… ሳይኪያትሪ አጠናለሁ ብዬ  ነበር የሄድኩት  እዛ እንደደረስኩ ግን ( ፖላንድ ) ማለታቸው ነው ሃሳቤን ለወጥኩ…

ምናልባት ቆዳ ከውበት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ብዬ ነው እኮ አልኳቸው ጨዋታችንን ለማራዘም፡፡

“ምን መሰለሽ ቆዳ የውስጥ ነጸብራቅ ነው ልክ ነሽ …ግን አንድ የቆዳ ህክምና የህጻናት፣ የስኳር፣ የውስጥ ደዌ ብቻ ምን ልበልሽ የሁሉም የጤና እውቀት ኖሮሽ ምትሰሪው ነው… ቆዳ ህክምና ሰፊ ነው የማትነኪው የጤና ጉዳይ የለም፡፡ እንዲያውም አንዳንድ አገሮች ቀጥታ የቆዳ ህክምና ትምህርት አይሰጡም ሃኪሙ በውስጥ ደዌ ስፔሻላይዝ ማድረግ አለበት … ቆዳ ህክምናን ስመርጥ በአገራችን ያለውን የህክምና እጥረት በማየቴና የድኅረ ምረቃ ትምህርት ቤትም እከፍታለሁ ብዬ በማሰብ ነው” አሉኝ፡፡

ህክምናው በድሮ ዘንድሮ…

ምንም እንኳን በአለርት ሆስፒታል የቆዳ ህክምና ይሰጥ የነበረ ቢሆንም በብዛት የሚያተኩረው በስጋ ደዌ ላይ ነበር፡፡ የህክምና ባለሞያዎቹም በአብዛኛው የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ የሚሰሩትም አዲስ አበባ ላይ ነው … ወሎና ሃረር ላይም በስጋ ደዌ ህክምና አጭር ስልጠና እየተሰጣቸው የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ነበሩ… እነሱም ቢሆኑ የተሟላ እውቀት ኖሮአቸው አልነበረም የሚያክሙት የቻሉትን ያክል ሰርተው ወደ አዲስ አበባ ነው ሪፈር የሚልኩት፡፡

“አስቢው እስቲ ስንት ሰው ነው አዲስ አበባ መጥቶ በወቅቱ ታክሞ የሚሄደው? …አብዛኛው በሽተኛ ገንዘቡን ጨርሶ በረንዳ አድሮ ተዘርፎ ነበር ወደ አገሩ የሚመለሰው…ለዚህ ነው የድህረ ምረቃ ያስፈልጋል ብዬ የተነሳሁት” አሉኝ፡፡ዶ/ር ዳኛቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ሲያስተምሩና ሲያክሙ ኖረዋል የቆዳ ህክምና ስፔሻሊቲ ዲፓርትመንትን  ለመክፈት ግን አስር ዓመታት አስጠብቋቸዋል ፡፡

እንዳሉኝ ከሆነ የቆዳና አባለዘር ህክምናን በውጪ አገር ተምሮ መምጣት ይቻላል ግን የአገራችንና የውጪው የቆዳ ጤና ችግር ይለያያል የእኛ በአብዛኛው ትሮፒካል የሚባል አይነት ነው… ስለዚህ በአገራችን የህክምና ትምህርቱ ቢሰጥ የበለጠ ህብረተሰቡን መጥቀም ይቻላል ወጪንም ይቀንሳል፡፡

የአገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንደማለት…

ዶ/ር ዳኛቸውን በቆዳ ህክምና ቀዳሚና ብቸኛ ሃኪም ነበሩ ባንልም በ80 ዎቹ አጋማሽ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሲሰሩ ግን ቀዳሚ ናቸው፡፡

 የድህረ ምረቃ ትምህርት …

አንድ ሰው ብቻውን የህክምና ክፍል ከፍቶ ማስተማር አይችልም ስርዓተ ትምህርት መቀረጽ አለበት… መምህራን መኖር አለባቸው ይህ ሁሉ እስኪሟላ አመታትን ፈጅቷል የኋላ የኋላ እ.ኤ.አ በ2006 የትምህርት ክፍሉ በህይወት የሌሉት ዶ/ር ዘውዱ በዜን ጨምሮ በስድስት መምህራን ስድስት ተማሪዎችን በመቀበል ጀምሯል፡፡

 ከጥቁር አንበሳ ዶ/ር ምህረት እና የአሁኑ የጳውሎስ ሚሊኒየምም ሆስፒታል ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶ/ር ዘሪሁን ከመጀመሪያዎቹ የዶ/ር ዳኛቸው ተማሪዎች ናቸው …ሁሉም በአገራቸው እያገለገሉ ነው፡፡ የትምህርት ክፍሉ በሚቀጥለው አመት አስረኛ ዙር ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ  የሃኪሙ ቁጥር መቶ ይደርሳል… አሁን ባለንበት በክልል ሪፈራል ሆስፒታሎች ቢያንስ ሁለት ሃኪሞች አሉ በአጭር ግዜም ቁወደ አምስት ከፍ ይላል፡፡

 ዶ/ር ቸኩለዋል…ባያነሱትም ብዙ ስልከ እየተደወለላቸው ነው…

“የጥቁር አንበሳ ድህረ ምረቃ ክፍል በሚቀጥለው አመት አጋማሽ ወደ ሰብ ስፔሻሊቲ ትምህርት ከፍልነት ያድጋል… ደርማቶ ፓቶሎጂ፣ ፔዲያትሪክስ ደርማቶሎጂ፣ ኮስሞቲክ ደርማቶሎጂ፣ ደርማቶ ሰርጀሪ እና ሌሎችም ላይ ሰብ ስፔሻሊቲ እንጀምራለን…  ይሄ ትልቅ ስኬታችን ነው” አሉኝ እንደምንም ባራዘምኩት ጨዋታችን ፡፡

እንደማልለቃቸው ሲያውቁ ነው መሰል ችኮላቸውን ቸል እያሉት ነው…

በጅማ፣ በመቀሌ፣ በሃዋሳ እና በባህርዳር የድህረ ምረቃ ትምህርት እንደሚሰጥም ነገሩኝ፡፡

በቆዳ እና አባለዘር ህክምና የትኛው በሽታ ነው ከባድ?  በሚቀጥለው