መጋቢት 28/2011 ኢ.ህ.ማ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ በሀገሪቱ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ `ለህክምና ባለሙዎች የተሰጠው ትኩረት በቂ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ያሰለጠናቸውን 42 ሐኪሞችን ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ በአሁን ሰዓት ከተለያዩ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ በርካታ ሰልጣች ቢኖሩም በመንግስት በኩል በህክምና ተቋማት መድቦ አለማሰራት አሳሳቢ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡
በተለይም ጥራት ያለው ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ ሀገሪቱ የሰለጠነ የህክምና ባለሙያ ብትፈልግም የባለሙያዎች ቅጥርን ለማከናወን ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ጥያቄ እንደሆነባቸው ነው የገለጹት፡፡
ለዚህ ደግሞ የሚመለከታቸው አካለት ትኩረት ሊያደርጉበት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
“አገራችንና ህዝባችን ገና ብዙ ሀኪሞችንና የጤና ድርጅቶችን እንደሚፈልግ ይታወቃልና እባካችሁ አሁን በመቶዎችና ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሀኪሞችን ስራ አጥ አታድረጓቸው፤ ጤና መሰረታዊ ፍላጎት ነው ከማለት አልፋችሁ በቂ በጀት በጅቱለት፤ በዚች ደሃ አገር ሀኪም ስራ አጥቶ ሰላማዊ ሰለፍ ወጣ ተብሎ መሳቂያ መሳለቂያ አንሁን እላቸዋለሁ፡፡”
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በተለይም የጤና ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ለመስጠት እያጋጠማቸው ያለውን ችግሮችና ለጤናው ዘርፍ ፈተና የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ፕሬዘዳንቶች ለማቅረብ መዘጋጀቱንም የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ገመቺስ ማሞ በምርቃቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ተማሪዎች በስልጠና ወቅት የሚጋጥማቸው የትምህርት መሳሪያዎች ግብኣት አለመሟላት ፤ የመምህራን እጥረት ዘርፉን ከመጀመሪው እየገጠመው ያለው ወሳኝ ፈታናዎች ናቸው ብለዋል፡፡
” የዛሬ ተመራቂዎች ፈተናዎችን አልፋችሁ ነው ለዛሬዋ ቀን የደረሳችሁት፡፡ ሌላው ቢቀር ባንድ ወቅት ተፈጥሮ የነበረው የአስተማሪ እጥረት እና በቅርቡ ተፈጥሮ የነበረው የኢንተርንሺፕ እሰጥ አገባ የሚረሱ አይደሉም፡፡”
Download the whole Speech
https://drive.google.com/open?id=1mCi4t36uni5H4QUG_XCz5aqABxHO6lAu