የህክምና ባለሙያው በስራ ቦታው ላይ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደርሱበት የተለያዩ አካላዊና ሞራላዊ ጥቃቶች እንዲሁም ተገቢነት የሌላቸው የህክምና ሃላፊነት ክሶች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ስራውን ተረጋግቶ እንዳይሰራ እያደረጉት ነው ፡ በተጨማሪም የህክምና ስህተት የሚመረመርበትና የሚዳኝበት የሕግ ስርአት የህክምና ሙያ ስራን የተለየ ባህሪ መሰረት ያደረገ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ በሃኪሞች ላይ በፍርድ ቤት የሚወሰነው ቅጣት የስራ ሞራላቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ፡፡ ስለሆነም ከህክምና አገልግሎት የወንጀል ሃላፊነት ጋር በተያያዘ በስራ ላይ ያሉት ሕጎች ተገቢው ማሻሻያ እንዲደረግባቸው
የታካሚና የህክምና ባለሙያ ግንኙነት አና የታካሚ መብትና ግዴታ የሚገዛ የህግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ እና ሁሉም ማህበረሰብ እንዲያዉቀዉ እንዲደረግ
የህክምና ባለሙያው በስራ ላይ ለሚገጥሙት ችግሮች ተመጣጣኝ የሆነ የካሳ ክፍያ ጥያቄ መልስ ይሆን ዘንድ የህክምና ባለሞያዎች የኢንሹራንስ ሽፋን ሊኖራችዉ ይገባል
የህክምና ባለሙያን መድቦ ለማሰራት ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ከዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሁም ሃገሪቱ ከያዘችዉ የጤናዉ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ እና መንግስት የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት ለማረጋገጥ ያለበትን ግዴታ የሚፃረር ስለሆነና የጤናውን ዘርፍ የሚጎዳ በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል፡፡
የሰውን ህይወት በኃላፊነት የተረከበ ሀኪም የሚከፈለው ደሞዝ ዝቅተኛ በመሆኑ ያለበትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም ፈተና ሆኖበታል፡፡ በመሆኑም የደሞዝ ማሻሻያ ጥያቄው ልዩ ትኩረት እንዲደረግበት የሚሉት ይገኙበታል ፡፡