ተመርቀው ስራ ያልያዙ ከ 450 በላይ የሚሆኑ የሃኪሞች ምደባ መካሄድ ጀመረ፡፡

ሚያዚያ 3/2011 ኢ.ሕ.ማ. የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ከዚህ በፊት ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ በርካታ ሰልጣኞችን በህክምና ተቋማት መድቦ አለማሰራት አሳሳቢ እንደሆነበት መግለጹ ይታወሳል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ችግሩ እልባት እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን በዛሬው እለት የጤና ሚኒስቴር ተመርቀው ስራ ያልያዙ ከ 450 በላይ ሃኪሞችን ምደባ ማካሄድ መጀመሩን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርም ለማወቅ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርም ለዚህ ውጤት መድረስ ሚና ለነበራቸው ፤ሀኪሞችን በመወከል ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩት ና ለጤና ሚንስቴር አመራሮች ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ማህበሩ የህክምና የባለሙያዎቹን የምደባ ሂደትና ከምደባ በኋላ በአግባቡ ስራ እንዲጀምሩ መደረጋቸውን በመከታተል ያሉትን ሁኔታዎችን የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡ የጤና ሚኒስቴርም ሀገሪቱ የሰለጠነ የህክምና ባለሙያ እንደሚያስፈልጋት ቢያምንም የባለሙያዎች ቅጥርን ለማከናወን የበጀት እጥረት እንዳለበት እንደ አንድ ምክንያት ሲጠቅስ ቆይቷል፡