በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ 8ኛ ቅርንጫፍ ተከፈተ

ኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ዛሬ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ስምንተኛ ቅርንጫፉን ከ 60 በላይ የሚሆኑ የህክምና ባለሞያዎች በተሳተፉበት ከፍቷል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝደንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ለጉባኤው ስለ ህክምና ማህበሩ ጠቅላላ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከጉባዔው የተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ ከ ጥያቄዎቹም ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሃኪሞች የሚከፈለው የዲዩቲ ክፍያ ወጥነት ሊኖረው ይገባል፣ የህክምና ትምህርትጥራት ላይ ማህበሩ ምን ሰራ፣የማህበሩ ህንጻ ለምን እስከ አሁን ሊሰራ አልቻለም፣ የሞያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት license ጉዳይ ለምን ማህበሩ አይዘውም የሚሉና ሌሎች ናቸው፡፡

 በአጠቃላይ ማህበሩ ወደ ክልሎች መውረዱን ጉባኤው ያስደሰተው ሲሆን ይወክሉናል ያሏቸውን
1. ዶ/ር ሙሉቀን አህመድ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት
2. ዶ/ር ይገረም አሰፋ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጸሃፊ
3. ዶ/ር ታዲዮስ ሃይሉ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የአባላት ጉዳይ
4. ዶ/ር ኩሴ ኮይሪታ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተከታታይ ህክምና ትምህርት 
5. ዶ/ር ተንትናይ ህዝቅኤል አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ገንዘብ ያዥ
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አድርጎ መርጧል፡፡